ነፀብራቅ ከገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም በላይ ነው!
የነፀብራቅ ሰብሳቢ በመሆኔ እንዲሁም ይህንን ማህበረሰብን የመለወጥ ራዕይ ይዞ የተነሳን ማህበርን በመምራቴ ትልቅ ክብር ይሰማኛል። በጋራ፣ እርስ በእርሱ የሚተማመን፣ በኢኮኖሚ የጎለበተ መሰረት ያለው ማህበረሰብ እየገነባን ነው። የአባላቶቻችን ቁርጠኝነት የማህበራችን እድገት እንዲያድግና እንዲቀጥል ትልቅ አስተዋፆኦ አድርጓል። በቀጣይ ማህበሩ ለአባላት የኢኮኖሚ ደጀን የመሆኑን እቅድ ከግብ እንዲያደርስ እንድትተባበሩን እጋብዛለሁ፡፡ ነፀብራቅ የቁጠባ እና ብድር ተቋም ብቻ ሳይሆነ የእድገት እና የለውጥ እንቅስቃሴ ነው፡፡ እንቆጥብ፣ እንበደር፣ እንደግ!!