ብድር ማለት አባላት ለተለያዩ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ የሚሆን ከቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር በሚደረግ ስምምነት መሰረት በተወሰነ ጊዜ ቆይታ ተመላሽ የሚሆን እና ወለድ የሚያስከፍል ወይም ወለድ የማያስከፍል ገንዘብ ነው፡፡
ማኅበሩ በቆጠቡት ላይ እስከ 4 እጥፍ ድረስ ያበድራል፡፡
ማኅበሩ ላበደረው የገንዘብ መጠን በየዓመቱ 12.5% እስከ 15.5%ያስከፍላል፡፡
አንድ አባል ብድር ለመጠየቅ በአባልነት 6ወር የቆየ መሆን አለበት፡፡
ለመበደር መግዛት የሚገባውን ዕጣ መግዛት ይኖርበታል፣
የብድሩን ቅድመ ቁጠባ አስቀድሞ ያለማቋረጥ በተከታታይ የቆጠበ፣
ገቢን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል፣
ለመበደር የሚፈልጉትን ገንዘብ 25% መቆጠብ ይገባል፡፡
ብድር የሚሰጠው የተበዳሪውን የመክፈል አቅም ባገናዘበ እና ባቀረበው ዋስትና መጠን ብቻ ነው፡፡
የጋብቻ ሁኔታን የሚገልፅ ስርተፍኬት የራሱንም ሆነ የዋሱን ማቅረብ የሚችል፣